የኢትዮጵያ ፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲትና ሌሎች የስራ ክፍሎች የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ በአፍሪካ የእንግሊዝኛ ተናጋሪ ሀገራት ዋና ኦዲተር ተቋማት ማህበር (AFROSAI-E) ስር ከሚገኙ ዋና ኦዲተር ተቋማት የተውጣጡ የኦዲት ኤክስፐርቶች የተሳተፉበትና በዋናነት በፋይናንሽያልና ህጋዊነት ኦዲት የአሠራር ማኑዋሎች ይዘቶችና አተገባበር ላይ ያተኮረው የምክክር ወርክሾፕ በርካታ ጠቀሜታ ያላቸው ልምዶችና ተሞክሮዎች የተገኙበት መሆኑ ተጠቆመ፡፡
ከነሀሴ 20 አስከ ጳጉሜን 1 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ሲካሄድ በነበረው ወርክሾፕ በዋናነት በፋይናንሽያልና ህጋዊነት ኦዲት የአሠራር ማኑዋሎች ይዘቶችና አተገባበር ላይ የሚስተዋሉ ጠንካራ ጎኖችና የታዩ ተግዳሮቶች ተነስተው ሰፊና ጥልቀት ያለው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በወርክሾፑ ቆይታ በቅድመ ኦዲት፣ በኦዲት ሂደትና የኦዲት ሪፖርት ዝግጅትና አቀራረብን ጨምሮ ከኦዲት በኋላ በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ልምዶችና ተሞክሮዎች ቀርበው ዝርዝር ውይይቶች መካሄዳቸው ታውቋል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤን በመወከል በወርክሾፑ ማጠናቀቂያ ላይ የተገኙትና የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የዋና ኦዲተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አወቀ ጤናው ወርክሾፑ የተለያዩ የማህበሩ አባል ሀገራት ዋና ኦዲተር ተቋማት የኦዲት አሠራር ልምዶችና ተሞክሮዎች የቀረቡበት በመሆኑ ለቀጠናው ሀገራት የኦዲት ተቋማት ወጥ የሆነና አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የኦዲት ስራ ለማከናወን ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል፡፡
ወርክሾፑ ከፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የፋይናንሽያልና ህጋዊነት ኦዲት የስራ ክፍሎች፣ ከኦዲት ጥራት ማረጋገጥ እና ከትምህርትና ስልጠና የስራ ክፍሎች የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎች የተሳተፉበት በመሆኑ ለተቋሙ የኦዲት አሠራርና የማኑዋሎች አተገባበር ከፍተኛ ግብአት የተገኘበት መሆኑን ጨምረው የገለጹት አቶ አወቀ ወርክሾፑን በማዘጋጀትና ገለጻ የሚያደርጉ ኤክስፐርቶችን በመመደብ ጉልህ አስተዋጽኦ ላደረገው ማህበሩ በፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ወርክሾፑን በመምራትና ገለጻ በማቅረብ የተሳተፉ የማህበሩ ኤክስፐርቶችና ከተለያዩ ሀገራት ኦዲት ተቋማት የመጡ የወርክ ሾፑ ተሳታፊዎች በበኩላቸው መድረኩ በማህበሩ ስር ለሚገኙ የተለያዩ ሀገራት ኦዲት ተቋማት አለምአቀፋዊ ስታንዳርዶችን የጠበቀና ወጥነት ያለው አሠራር እንዲኖር በማድረግ በኩል ድርሻው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው ኢትዮጵያ እንደሀገርና የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት እንደ ቀቋም የወርክሾፑን ቅድመ ዝግጅት ከማመቻቸት ጀምሮ እስከፍጻሜው ድረስ ለወርክሾፑ ስኬታማነት ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ከማህበሩ ስታፍ እና ከተለያዩ የማህበሩ አባል ሀገራት የዋና ኦዲተር ተቋማት የመጡትን ጨምሮ በወርክሾፑ ቆይታ ያደረጉ ተሳታፊዎች ከወርክ ሾፑ በተጓዳኝ ነሀሴ 25 ቀን 2016 ዓ.ም በአንድነት ፓርክ በመገኘት የኢትዮጵያን ታሪካዊ፣ ባህላዊና ሀገራዊ እሴቶችን ጎብኝተዋል።
The AFROSAI-E Workshop to bring meaningful Sharing Experiences for Audit Practices
OFAG፡ 7 Sep 2024:-The African Regional organization of English-Speaking Supreme Audit Institutions (#AFROSAI-E) workshop, held from August 26 to September 6/2024 in Addis Ababa, resulted to be very beneficial in sharing auditing experiences of different audit institutions across nations under AFROSAI-E.
The workshop that mainly focused on discussing the contents and implementation of financial and compliance audit manuals, commonly implemented in all audit institutions of AFROSAI-E, covered the entire financial and compliance auditing phases from the pre auditing tasks to the auditing reports.
The partakers of the workshop from different audit institutions of different African countries under AFROSAI-E including the audit and other appropriate officials of the Ethiopian Office of the Federal Auditor General indicate that they have shared vital auditing experiences each other, and such exchanging know-hows are significantly gainful to build their general auditing capabilities more, and to fill the gaps between the principles in the manuals and the practical implementations.
Mr. Aweke Tenaw, office head, in the office of the Ethiopian Auditor General, attended in the closing period of the workshop by representing H.E Meseret Damtie, the Ethiopian Auditor General, forwarded the benefits of the workshop by mentioning detail advantages to share auditing experiences of different institutions under AFROSAI-E.
With his grateful thanks to the staff of the AFROSAI-E and the participants of the workshop for their contribution to the success of the program, Mr. Aweke addressed that the working experiences and significant points discussed in the workshop are basic inputs to be more effort in order to strengthen the capacity of the auditing activities.
Besides the main schedule of the workshop, the participants also made visit the national Unity Park to observe the historical and cultural heritages of Ethiopia.