News

በክዋኔ ኦዲት ጥራት ማስጠበቅ ላይ ያተኮረ ወርክሾፕ ተካሄደ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለመ/ቤቱ የክዋኔ ኦዲተሮች ከመጋቢት 22/2017 ዓ.ም ጀምሮ 5 ቀናትን የፈጀና በክዋኔ ኦዲት ጥራት ማስጠበቅ ላይ ያተኮረ ወርክሾፕ አካሄደ

ወርኮሾፑን በይፋ ያስከፈቱት የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ የወርክሾፑ ዓለማ በክዋኔ ኦዲት የሥራ ማንዋሎች ላይ ተጨማሪ ግንዛቤ ለመፍጠር እና በኦዲት ሥራ ወቅት ከእቅድ እስከ ሪፖርት የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት የኦዲት ጥራትን ይበልጥ ለማሳደግ መሆኑን ገልጸው የመ/ቤቱ የኦዲት ስራ  የኦዲት ሽፋንን ከማሳደግ ባለፈ የኦዲት ጥራትን ማረጋገጥ መሠረታዊ ጉዳዩ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

መድረኩ የወርክሾፑ ተሳታፊዎች  ከመድረክ ከሚያገኙት ገለጻ ባለፈ በሥራ ወቅት ያጋጠሟቸውን ችግሮች በማንሳት ውጤታማና ሰፊ ውይይት ያደረጉበት መሆኑ ታውቋል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በየጊዜው የኦዲተሮችን አቅም ለማጎልበት ተከታታይ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን እያካሄደ ሲሆን  ወርክሾፑ ከ100 በላይ የክዋኔ ኦዲተሮችን በተለያዩ ዙሮች ያሳተፈ እንደነበር ከትምህርትና ሥልጠና ዳይይክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *