በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሬዲዮና ቴሌቭዥን ማስፋፊያና ማሻሻያ ፕሮጀክት አፈፃፀምና ከአናሎግ ወደ ዲጂታል የሚያደርገውን ሽግግር በተመለከተ ከ2001-2006 በጀት ዓመት በተደረገው የክዋኔ ኦዲት ግኝቶች ሪፖርት ላይ ይፋዊ ስብሰባ /Public Hearing/ ግንቦት 22 ቀን፣ 2008 ዓ.ም አካሄደ፡፡
በፌዴራል ዋና ኦዲተር (ፌዋኦ) መ/ቤት በቀድሞው የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት በአሁኑ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ላይ ባደረገው የክዋኔ ኦዲት ግኝት እንዳመለከተው ኮርፖሬሽኑ የሬዲዮና የቴሌቭዥን ማስፋፊያና ማሻሻያ ፕሮጀክት ለሬዲዮና ቴሌቭዥን ጣቢያዎቹ በሚያስፈልጋቸው መሠረት ቢያሰራም የተለያዩ ችግሮች እንደታዩበት አመልክቷል፡፡ ለዚህም እንደማስረጃነት ለአብነት ኦዲት በተደረጉ ጣቢያዎች ውስጥ በድሬዳዋ የቴሌቭዥን ጣቢያ ጽ/ቤትና የማሰራጫ ትራንስፎርሜሽን የተገነባበት ቦታ የሲሚንቶ ፋብሪካ የጥሬ ዕቃ ማምረቻ ክልል ውስጥ መሆኑ፣ የጣቢያው መስታወቶች መሰባበራቸውና ግድግዳው በመሰነጣጠቁ ዝናብ እያስገባ መገኘቱን፤ የደሴ የቴሌቭዥን ማሰራጫ ጣቢያ የተገነባበት ቦታ ለመድረስ የሚያስችል መንገድ አለመሠራቱን፤ የጮቄ ተራራ ማሰራጫ ጣቢያ የተገነባበት ቦታ ርቀት ያለውና የመብራት አገልግሎት የሌለው መሆኑን በኦዲቱ ጠቅሷል፡፡
በሌላ በኩል የኦዲት ሪፖርቱ እንደተመለከተው የፕሮጀክቶች የቴክኖሎጂ ተከላ፣ ማሰራጫ፣ የዕቃ አቅርቦት የሲቪል ግንባታና የኮሚሺኒግ ሥራ ለመከታተልና ለመቆጣጠር የሚያስችል የፕሮጀክት ሥራ አመራር መመሪያ የመንግስትና የኮርፖሬሽኑን የፕሮጀክት አዘገጃጀት መመሪያ በተከተለ መልኩ አለመዘጋጀቱን በኦዲት ግኝቱ ገልጿል፡፡
ከሀገር አቀፍ የሬዲዮና ቴሌቭዥን ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች የመሣሪያ ግዢ፣ የህንፃ ግንባታውና የማሰራጫ መሣሪያዎቹ ተከላ በስተቀር ሌሎቹ ወጪዎች በጥናቱ ለፕሮጀክቱ ከተመደበው ወጪ ከፍተኛ ብልጫ (58 በመቶ) ማሳየቱን እንዲሁም ፕሮጀክቶቹም በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ አለመጠናቀቃቸውን የኦዲት ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡
ከቴክኖሎጂ መትከል ጋር በተያያዘ ኮርፖሬሽኑ የቴክኖሎጂ ገጠማውን ለማከናወን በድርድር እንዲሠራ የመረጠው ኮንትራክተር (China Poly Technolopgies Inc) የተመረጠበት ዝርዝር መስፈርት አለመቅረቡን፣ በሁለተኛው ዙር የፕሮጀክት አፈጻጸም ግምገማ የ32 ጣቢያዎች ፕሮጀክቶች እንዲሁም የሁሉም ታወር ግንባታዎች የክትትልና ቁጥጥር ሥራ ለኮንትራክተሮቹ የተተዉ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም የቴክኖሎጂ ግንባታቸው ተጠናቆ ርክክብ ከተፈፀመላቸው 8 ማሰራጫዎች የተበላሹ ጄኔሬተሮች፣ ኮንትሮል ዩኒት (Control Unit)፣ ኤር ኮንዲሽነር (AC)፣ ኤቪአር (AVR)፣ እና ኤክሳይተር (Exciter) መኖራቸው እና በድሬዳዋ፣ ደሴ፣ ወልዲያ፣ ባህር ዳር፣ ጮቄና አመንቲላ ማሰራጫ ጣቢያዎች ዩፒኤስ (UPS) የሌላቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡
ከዘመናዊ የአርካይቭና ኢዲቲንግ ሥራ ጋር ተያይዞ ሥራው አለመጠናቀቁን፤ የፕሮዳክሽን ሥራዎች ደህንነታቸው በተጠበቀ ሁኔታ አለመከማቸታቸውን እና የፕሮዳክሽንና የማስተዋወቅ ሥራ አለመሰራቱን እንዲሁም ደካማ የቁጥጥር ሥርዓት መኖሩን የኦዲት ግኝቱ ጨምሮ አብራርቷል፡፡
የሬዲዮና ቴሌቭዥን ሥርጭትን ከአናሎግ ወደ ዲጂታል ለማሸጋገር በስትራቴጂክ ዕቅድ የተያዘና የዲጂታላይዜሽን ትግበራ ስትሪንግ ኮሚቴ በ2003 ዓ.ም የተቋቋመና የሬዲዮና የቴሌቭዥን ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች በሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ስርጭት እንደሚጀምር በፕሮጀክቱ ፕሮፖዛል ላይ የተገለፀ ቢሆንም ሽግግሩ በተቀመጠው ጊዜ እንዳልተፈፀመ ተገልጿል፡፡
በማስፋፊያና ማሻሻያ ፕሮጀክት ጥናት ፕሮፖዛልና በ5 ዓመቱ (2003-2007 ዓ.ም) ስትራቴጂክ ዕቅድ የትራንስሚተሮችን ተከላ እስከ 2004 ዓ.ም ተግባራዊ በማድረግ የሬዲዮ ሽፋንን ከ75 በመቶ ወደ 95 በመቶ የቴሌቭዥን ሥርጭትን ደግሞ ከ55 በመቶ ወደ 86 በመቶ ለማድረስ እንዲሁም የዲጂታል ስርጭትን በየካቲት 2005 ዓ.ም ለመጀመር ቢታቀድም አፈፃፀሙ በሁለት ዓመታት የዘገየ መሆኑና አስፈላጊ የዲጂታል ሥርጭት የመቀበያ መሣሪያዎች አለመሟላታቸውን የኦዲት ሪፖርቱ አትቷል፡፡
የኦዲት ሪፖርቱን መሠረት አድርገው በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ ምላሽ የሰጡት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃነ ኪ/ማርያም የኦዲት ሪፖርቱን እንደሚቀበሉና የኦዲት ግኝቱን መሠረት አድርገው ለማስተካከል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
ሌሎች የኮርፖሬሽኑ አመራሮች ምላሽ ሲሰጡ የኦዲት ግኝቱ በክልል ያሉ ሬዲዮ ማሰራጫ ጣቢያዎች የመንገድ ችግር ያለባቸውና በተራራ ላይ የሚገኙ በመሆናቸው አስቸጋሪ የትራንስፖርት ሁኔታ እንዳለ ገልፀው ይህን ችግር ለመቅረፍ በተደረገ ጥረት ከደሴ ከተማ አስተዳደር ጋር በመነጋገር መንገዱ እንዲስተካከል ማድረጋቸውን፤ አሁንም ድረስ የጮቄ ተራራ ማሰራጫ ጣቢያ መብራት ስለሌለው በጄነሬተር እንደሚሠራ እና በአርካይቭ በኩል የዲጂታል አርካይቭ ፕሮጀክት በማዘጋጀት ከ100 ሺ ሰዓት በላይ ያለው ፋይል እንዲከማች መደረጋቸውን አስረድተዋል፡፡
የሬዲዮና የቴሌቪዥን ማስፋፊያ ከተመደበው 58 በመቶ ብልጫ ያሳየው ፕሮጀክቱ ሲታቀድ ለዕቃዎች ግዢ የተያዘው ገንዘብ በውጭ ምንዛሪ መናር ምክንያት ተጨማሪ ወጪ በመጠየቁ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ ከዩፒኤስ (UPS) ጋር በተያያዘም በዋና ማሰራጫ ጣቢያ የነበረውን የኃይል መቆራረጥ ችግር ለመቅረፍ በማሰብ ከማሰራጫ ጣቢያዎች መወሰዳቸውን እና በዚህ ምክንያት የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ለማሰራጫ ጣቢያዎች ዩፒኤስ ከውጭ ተገዝተው እንዲገቡ እየተደረገ እንደሚገኝና በቅርቡ ችግሩ እንደሚፈታ አስረድተዋል፡፡
ክቡር ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዲቢሶ ሲገልፁ ኮርፖሬሽኑ ከኦዲት ግኝቱ በኋላ ግብረመልሱን መሠረት አድረጎ የሰራው ሥራ ጥሩ መሆኑን ገልፀው ነገር ግን ኮርፖሬሽኑ ዕቅዱን ሲያቅድ ከአናሎግ ወደ ዲጂታል እንደሚሸጋገሩና ያንንም ለመሥራት እንደተዘጀ ቢገለፅም ተግባራዊ ለማድረግ እንደልቻለና ከተመደበ ገንዘብ በላይ ወጪ የተዳረገውም ፕሮጀክቱ በአግባቡ ባለመታቀዱ እንደሆነ ገልፀው በተገኙት የኦዲት ግኝቶች ላይ ተቋሙ ትኩረት ሰጥቶ ሊሠራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክቡር አምባሳደር መስፍን ቸርነት ለሥራው ማጓተት የፕሮጀክት አመራር ጽ/ቤት አለመደራጀት እንዲሁም በሥራ መመሪያ አለመኖር ምክንያት የተከሰተ በመሆኑ ኮርፖሬሽኑ ለነዚህ ጉዳዮች ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በየክልል ጣቢያዎች ላይ ለሚታዩ ችግሮች የክትትልና ቁጥጥር ችግር መኖሩን እንደሚያሳይና ተቋሙ ከፖሊሲና እስተራቴጂክ ዕቅድ አንጻር እያየ ሊከታተል እንደሚገባ ገልጸው ተቆጣጠሪ መ/ቤት የሆነው የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣንም እየተሠራ ያለው ሥራ ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታና በአግባቡ መከናወኑን መከታተልና መቆጣጠር እንዳለበት
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከአናሎግ ወደ ዲጂታል የሚያደርገው ሽግግር መዘግየቱ ተገለፀ