News

የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች በሚታየው አለመረጋጋት ሳይረበሹ በገለልተኝነት ለላቀ የኦዲት ጥራት መስራት እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡

የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች በሚታየው አለመረጋጋት ሳይረበሹ በገለልተኝነት ለላቀ የኦዲት ጥራት መስራት እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡

 

የፌዴራል ዋና ኢዲተር መ/ቤት ሰራተኞች በቅርቡ በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች በተከሰተው አለመረጋጋት ሳይረበሹ ተቋሙ የተጣለበትን ሀገራዊ ተልዕኮ ለማሳካት በገለልተኝነትና በላቀ የስራ መንፈስ መስራት እንደሚኖርባቸው ዋና ኦዲተር ክቡር አቶ ገመቹ ዱቢሶ ነሀሴ 09 ቀን 2008ዓ.ም በተቋሙ መሰብሰቢያ አዳራሽ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙርያ ከሰራተኞች ጋር በተደረገ ውይይት ላይ ገለጹ፡፡

በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች እየተደረጉ ካሉት ሰላማዊ ሰል_dsc0335ፎች ጋር በተያያዘ መንግስት ከመልካም አስተዳደርና ሌሎች ጉዳዮች ጋር ለተያያዙ የህዝቡ ጥያቄዎች በተለያዩ አግባቦች ምላሽ ለመስጠት ጥረት እያደረገ መሆኑን ዋና ኦዲተሩ ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ገለልተኛ የዲሞክራቲክ ተቋም እንደመሆኑ መጠን በሀገሪቱ ውስጥ የግልጽነትና ተጠያቂነት ስርዐት እንዲሰፍን፣ መልካም አስተዳደር እንዲረጋገጥና የቁጥጥር ስርዐቱ እንዲጠናከር ያለበትን ልዩ ሀገራዊ ተልዕኮ ለማሳካት ሰራተኛው በወቅቱ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ገለልተኛ በመሆን ሙያዊ ግዴታውን በእይታና በተግባር በመወጣት ከቀድሞው የላቀ ጥልቀትና ጥራት ያላቸውን የኦዲት ግኝቶችን ማስገኘት እንዳለበት ገልጸዋል፡፡   

በተጨማሪም ዋና ኦዲተሩ ሰራተኛው ወቅታዊ ሁኔታው በፈጠረው አለመረጋጋት አማካኝነት ሊደርሱ ከሚችሉ ችግሮች ራሱን መጠበቅ እንዳለበት ገልጸው ከኦዲት ስራ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ ወቅታዊ ሁኔታው የሚፈጥራቸው ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን የተመለከቱ መረጃዎችን በቅርበትና በፍጥነት ከቅርብ የስራ ሀላፊዎች ጋር በመለዋወጥ ችግሮችን አስቀድሞ መከላከልና አስፈላጊው የስራ ለውጦችና ድጋፎች እንዲደረጉ ማስቻል እንዲሁም በኦዲት ተደራጊ መ/ቤቶች የሚፈጠሩበትን እክሎች ማሳወቅ እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡

ተቋሙ እየፈጠረው ያለው ተጽዕኖና ተሰሚነቱ ከመቼውም ጊዜ እየላቀ እንደመጣ የገለጹት ዋና ኦዲተሩ   ተጽዕኖው በቀጣይም እንዲያድግ ሰራተኛው በወቅታዊ ሁኔታዎች ሳይረበሽ የመ/ቤቱን ተልእኮ ለማሳካት የበለጠ መስራት እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡

_dsc0332መጨረሻም ክቡር አቶ ገመቹ የተቋሙ የ2008 በጀት አመት የኦዲት እቅድ ታህሳስ 30 ቀን 2009ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ታሳቢ በማድረግ እቅዶች በተያዘላቸው ጊዜ ሙሉ በሙሉ እንዲሳኩ ማድረግ እንደሚገባና ለዚህም አዲስ ተቀጣሪ ሰራተኞች የበኩላቸውን ሚና መጫወት እንዳለባቸው አስገንዝበው የመስሪያቤቱ የስራ ሀላፊዎችም ለሰራተኞች የስራ እንቅስቃሴ የሚያስፈልጉ ሁኔታዎችን ማሟላት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *