News

የልምድ ልውውጥ መድረክ ተካሄደ

የልምድ ልውውጥ መድረክ ተካሄደ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራትና ከኢንዶኔዥያ መንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር የልምድ ልውውጥ መስከረም 13 ቀን 2009ዓ.ም በተቋሙ ኮንፈረንስ ክፍል ውስጥ አካሄደ፡፡

_dsc0009መድረኩ በኦዲት ዘርፍ መ/ቤቱ ያለውን ተሞክሮ ለሌሎች ማጋራትንና ከሌሎች ሀገራት ልምድ መቅሰምን ያለመ ነበር፡፡

በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የዋና ኦዲተሩ ልዩ ረዳት የሆኑት አቶ ሻሾ መኮንን ለመድረኩ ተሳታፊዎች በመ/ቤቱ እንቅስቃሴዎች ዙርያ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን በዋናነት ከስልጣኑና ከኃላፊነቱ፣ ከሚያከናውናቸው የኦዲት አይነቶች፣ ከሚከተላቸው የኦዲት ስታንዳርዶች፣ ከሚያቀርባቸው የኦዲት ሪፖርቶች፣ ከስኬቶቹ፣ ከተግዳሮቶቹና ከወደፊት አቅጣጫዎቹ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡  አቶ ሻሾ በገለጻቸው ወቅት መ/ቤቱ መሰረታዊ የለውጥ ትግበራን ማካሄድ ከጀመረ ወዲህ የኦዲት ሽፋኑ እያደገ እንደመጣና ይህም በሀገሪቱ ውስጥ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዳደረገ አስረድተዋል፡፡

ተሳታፊዎች በተደረገላቸው ገለጻ ስለመ/ቤቱ እንቅስቃሴ በቂ ግንዛቤ እንደጨበጡ ገልጸዋል፡፡ መድረኩ አዲስ አበባ የሚገኘው የኢንዲኔዥያ ኤምባሲ ለፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት የተዘጋጀ ሲሆን ከኬንያ፣ ከታንዛኒያ፣ ከናይጄርያ ከቱኒዝያና ከኢንዶኔዥያ የተወጣጡ ኦዲተሮችና ዲፕሎማቶች ተካፍለውበታል፡፡

_dsc0019 _dsc0020

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *