News

የህግ ጽንሰ ሀሳብና ትግበራ ሂደትን የሚመለከት ስልጠና ተሰጠ

ለፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የልዩ ኦዲት ዳይሬክቶሬት የስራ ኃላፊዎችና ኦዲተሮች ስለ ህግ ምንነትና አተገባበር ሂደት ስልጠና ተሰጠ፡፡

ከጥቅምት 18 -19 ቀን 2017 ዓ.ም ለሁለት ቀናት በተሰጠው ስልጠና አስራ አምስት የሚሆኑ የዳይሬክቶሬቱ የስራ ኃላፊዎችና ኦዲተሮች የተሳተፉ ሲሆን ስልጠናው በማስረጃ ህግ ምንነት እንዲሁም በማስረጃ አሰባሰብና የሙያ ምስክርነት አሰጣጥን በተመለከተ መከናወን ባለባቸው ዝርዝር ሂደቶች ላይ ያተኮረ መሆኑ ታውቋል፡፡

በስልጠናው መክፈቻ ላይ በመገኘት ስልጠናውን የከፈቱት የመ/ቤቱ የዋና ኦዲተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አወቀ ጤናው ሲሆኑ የስልጠናውን ዓላማና ፋይዳ በተመለከተ ንግግር አድርገዋል፡፡

ስልጠናው በእርስ በእርስ መማማር ላይ የተመሰረተና  በስራ ሂደት የተገኙ ልምዶችንና ተሞክሮዎችን ልውውጥ ለማድረግ ጠቃሚ መሆኑን በመክፈቻ ንግግራቸው የገለጹት አቶ አወቀ ልዩ ኦዲት በዋናነት ተጠያቂነትን በተጨባጭ ለማረጋገጥ ያለው ፋይዳ የጎላ በመሆኑ ስልጠናው የልዩ ኦዲት ኦዲተሮች በህግ በተያዙ ጉዳዮች ላይ ለሚመለከተው የህግ አካል ለሚሰጡት ምስክርነት አጋዥ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ስልጠናው በመ/ቤቱ የህግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የተሰጠ ሲሆን የስልጠናው ተሳታፊዎች ስልጠናው በልዩ ኦዲት የስራ ሂደት የሚያጋጥሙ የህግ ክፍተቶችን ከመሙላት አንጻር ጉልህ ድርሻ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *