የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ከዩናይትድ አረብ ኢሜሬትስ ዋና ኦዲተር ተቋም ኃላፊ የተከበሩ ሐሚድ አቡሺቢስ ጋር ጠቃሚ የሆነ የስራ ውይይት አደረጉ፡፡
ክብርት ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ በነበራቸው ቆይታ ከተቋሙ አካውንተብሊቲ አውቶሪቲ ኃላፊ የተከበሩ ሐሚድ አቡሺቢስ ጋር ሁለቱ ተቋማት በጋራ በሚሰሩባቸው የኦዲትና ተዘማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም የሁለቱ ሀገራት ዋና ኦዲተር ተቋማት ወደፊት በሚያከናውኗቸው የጋራ ስራዎችና የልምድ ልውውጦች በተለይም የሥልጠና ማዕከላትን ማበልፀግን ጨምሮ በአቅም ግንባታ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኦዲት፣ የተለያዩ ወርክሾፖችንና ሴሚናሮችን በማዘጋጀት እና በሌሎች ተዛማጅ ኦዲትን በሚመለከቱ የስራ ዘርፎች ዙሪያ አብሮ ለመስራትና ለመደጋገፍ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።
የሁለቱ ሀገራት ዋና ኦዲተር ተቋማት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በውይይታቸው መጨረሻ የስምምነት ትግበራውን የሚያመቻችና የሚከታተል የቴክኒክ ኮሚቴ በቀጣይ ለማቋቋም ከስምምነት ላይ መድረሳቸውም ታውቋል፡፡
The Federal Auditor General’s Vital Discussion with the Head of the Accountability Authority of SAI UAE
The Ethiopian Federal Auditor General H.E Meseret Damtie made a significant bilateral discussion with the Head of the Accountability Authority of SAI United Arab Emirates-UAE, H.E. Humaid Abushibs.
In her occurrence in the United Arab Emirates, H.E Meseret exchanged basic issues on mutual Auditing working areas with H.E Humaid Abushibs and they agreed to work together in the coming time for their common advantages.
Information indicates that both officials, in their advantageous discussion, agreed to work together and share their working experiences in the areas of information technology audits, and capacity building including developing auditing training centers, organizing workshops & seminars, and also other related auditing practices.
In their final statement of the discussion, they reached an agreement to establish a technical committee that facilitates and monitors the implementation of the bilateral working proposal.