በስርዓተ-ፆታ ማካተት እና ምቹ የሥራ አከባቢ መፍጠር ዙሪያ የሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ለተቋሙ ሠራተኞች ግንቦት 3 ቀን 2009 ዓ.ም ሥልጠና ሰጠ፡፡
በሥልጠናው መግቢያ ላይ የሴቶችና ወጣቶች ዳይሬክተር ወ/ሮ ሙሉ ጥሩነህ እንደገለፁት ሥልጠናው በተቋሙ ያለውን የስርዓተ-ፆታ ማካተት በሚፈለገው ደረጃ እንዲገኝ ለሚሠራው ሥራ ግንዛቤ መፍጠሪያና ለትግባራዊነቱ አቅም የሚፈጠርበት መድረክ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
በስርዓተ-ፆታ ምንነት፣ አስፈላጊነትና አተገባበር ዙሪያ የሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ገዛኸኝ ሙሊሣ ማብራሪ የሰጡ ሲሆን በገለፃቸውም የተለያዩ አገሮች ተሞክሮዎችንና በአሁኑ ወቅት በአብዛኛው የዓለም አገራት እየተተገበሩ ያሉ የስርዓት-ፆታ አተገባበሮች ላይ በተለያዩ ገላጭ ማሳያዎች ለሠራተኛው አስረድተዋል፡፡
የስርዓተ-ፆታ ሥራን በተቋም ውስጥ አካቶ እንዴት ሊታቀድ እንደሚችልና በእቅዱ ሊካተቱ እንደሚገቡ እንዲሁም በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ባሉት ዳይሬክቶሬቶች ስርዓተ-ፆታ አካቶ ማቀድ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በማሳያነት በማቅረብ እና እቅዶቹ ያሉባቸውን ጥንካሬና ደካማ ጎን በማንሳት የስርዓተ-ፆታን ትግበራ ይበልጥ በመ/ቤቱ ውስጥ ውጤታማ በሚሆንበት አግባብ ላይ ወ/ሮ ሙሉ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በሥልጠናው የተሣተፉ ሠራተኞችም ሥልጠናው ጠቃሚ መሆኑን ገልፀው የስርዓተ-ፆታን እኩልነት ለማረጋገጥና የታቀደውን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ከፈፃሚው አካል በበለጠ በከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት ያሉ አመራሮች ቢሣተፉ በእቅድ አካቶ ለመተግበር የተሸለ በመሆኑ በመሰል መድረኮች ላይ የአመራሩ ተሣትፎ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
0 thoughts on “ከስርዓተ-ፆታ ማካተት እና ምቹ የሥራ አከባቢ ዙሪያ ሥልጠና ተሠጠ”
ስርዓተ ፆታን በየወረዳው ባሉ ሴክተሮች ለማካተት ያመች ዘንድ የተሸለ ጥናታዊ ጽሁፍ በአማርኛ የተየረ ብትልኩልን በጣም እናመሰግናለን