News

በኦዲትና በመ/ቤቱ የሚድያ ፖሊሲ ዙሪያ ለሚዲያ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት መገናኛ ብዙኃን በኦዲት ምንነትና አሰራር እንዲሁም መ/ቤቱ በሚያከናውናቸው ሥራዎች ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግና የተሻለ የኦዲት ዘገባ እንዲያዘጋጁ ለማገዝ ያለመ ሥልጠና ለሚዲያ ባለሙያዎች ግንቦት 18 ቀን 2009 ዓ.ም ሰጠ፡፡

በውጭና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው ስልጠና መክፈቻ ላይ ምክትል የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ መ/ቤቱ በክዋኔና በፋይናንሻል ኦዲቶች መስክ አበረታች ውጤቶችን እያስመዘገበና መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና የመንግሥትን የአፈፃፀም ብቃት ለማሳደግ እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

OFAG Ethiopia Training (2)ክብርት ም/ዋና ኦዲተሯ መ/ቤቱን እነዚህን አበረታች ውጤቶች እያስመዘገበ ቢሆንም በሕዝቡና በባለድርሻ አካላት በኩል መታወቅ በሚገባው ልክ እንዳልታወቀ ተናግረዋል፡፡ እንደዚሁም መ/ቤቱ በየወቅቱ የሚያወጣቸው የኦዲት መረጃዎችና ሪፖርቶች በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ለኅብረተሰቡ እንዲደርሱና የባለድርሻ አካላት የመ/ቤቱን የሥራ እንቅስቃሴ በአግባቡ በመረዳት ለተልዕኮው መሳካት እገዛ እንዲያደርጉ ለማድረግ የተሰራው ሥራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ ቢመጣም መድረስ በሚገባው ልክ እንዳልደረሰ ገልጸዋል፡፡

እስከአሁን በተደረገው እንቅስቃሴ ብዙኃን መገናኛዎች ላደረጉት አስተዋጽኦ መ/ቤቱ እውቅና እንደሚሰጥ የገለጹት ክብርት ወ/ሮ መሠረት የግልፅነትና ተጠያቂነት ሥርዓቱን ለማጠናከርና ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ከሚዲያ አካላት ጋር የበለጠ ተቀራርቦና ተደጋግፎ መሥራት ወሳኝ እንደሆነ መ/ቤቱ ይገነዘባል ብለዋል፡፡ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩም በዚህ ምክንያት የተዘጋጀ መሆኑንና መድረኩ የግንኙነቱ መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ እንዳልሆነም ተናግረዋል፡፡

OFAG Ethiopia Training (3)በስልጠናው ላይ ከኦዲትና መ/ቤቱ ከሚያከናውነው የኦዲት ስራ ጋር በተያያዙ ዋና ዋናጉዳዮች ላይ የጋራ አገልግሎቶች ክዋኔ ኦዲት ዳይሬክተር አቶ ጳውሎስ ዘሪሁን እና የኦዲት ጥራት ማረጋገጥ ዳይሬክተር አቶ አህመድኑር ሱዋሊህ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን በመ/ቤቱ የሚዲያ ፖሊሲ ላይም አቶ አወቀ ጤናው የውጭና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ገለፃ አድርገዋል፡፡ በተደረገው ገለጻ ዙርያ የሚድያ ባለሙያዎቹ አስተያየቶችን የሰጡ ሲሆን ላቀረቧቸው ጥያቄዎችም ምላሽ ተሰጥቷል፡፡ የሚድያ ባለሙያዎቹ ስልጠናው ስለኦዲትና በመ/ቤቱ ስለሚደረገው የኦዲት ስራ የነበራቸውን ግንዛቤ እንዳሳደገላቸው ገልጸዋል፡፡

በስልጠናው ላይ ከመንግሥትና ከግል የኤሌክትሮኒክስና የህትመት ሚዲያ የተውጣጡ 12 የሚዲያ ባለሙያዎች ተካፍለዋል፡፡

OFAG Ethiopia Training (5) OFAG Ethiopia Training (4)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *