የፌዴራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ እና ም/ዋና ኦዲተር ክቡር አቶ አበራ ታደሠን ጨምሮ ከመ/ቤቱ የማኔጅመንት አባላት የተውጣጡ አመራሮች በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ቅጥር ግቢ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ የመትከል መርሀ ግብር አካሂደዋል፡፡
ይህ ችግኝ የመትከል መርሀ ግብር “600 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀምበር” በሚል ነሀሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ የተካሄደውን ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ምክንያት በማድረግ ከመ/ቤቱ የማኔጅመንት አባላት የተውጣጡ አመራሮች በድጋሜ ያካሄዱት ነው፡፡
ቀደም ሲልም መላው የመ/ቤቱ አመራሮችና ሠራተኞች ሀምሌ 12 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 የካ ጣፎ ኮንዶሚንየም ልዩ ስሙ ጮሪሶ 2 በተባለው ስፍራ “የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ የተካሄደውን የአረንጓዴ አሻራ የማኖር ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ምክንያት በማድረግ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ የመትከል መርሀ ግብር ማካሄዳቸው የሚታወስ ነው፡፡
Seedling planting Program in the Office Compound
OFAG: 23 August 2024:- The Federal Auditor General H.E Meseret Damtie Chaniyalew & Deputy Auditor General H.E Abera Tadesse with some other management members of the Ethiopian Office of the Federal Auditor General, planted varieties of seedlings in the office compound.
Information indicates that the seedling planting program carried out by some members of the management was based on the nationwide schedule of planting `#600_million_seedlings_in_a_day` and, it was also additional planting deed of the office next to similar green legacy program accomplished months ago by the whole staff of the office around Lemi Kora Sub city of Addis Ababa City Administration under the nationwide motto of `A nation that plants with the generation that sustains’.