News

በተሻሻለው የክዋኔ ኦዲት ማኑዋል ላይ ያተኮረ ስልጠና ተጀመረ

በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በቅርቡ አዳዲስ የክዋኔ ኦዲት የአሠራር ይዘቶችን በማካተት የተሻሻለውን የክዋኔ ኦዲት ማኑዋልና የተሻሻሉትን ይዘቶች ለኦዲተሮች ለማስተዋወቅ የሚረዳ ስልጠና ተጀመረ፡፡

መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም በክቡር አቶ ሀጂ ኢብሳ የመ/ቤቱ የክዋኔ ኦዲት ዘርፍ ም/ዋና ኦዲተር የተከፈተው ስልጠና እስከ መስከረም 16 ቀን 2018 የሚቆይና በሁለት ዙሮች የሚካሄድ ሲሆን በጠቅላላው 60 የሚሆኑ የክዋኔ ኦዲት የስራ ኃላፊዎችና ኦዲተሮች የሚሳተፉበት መሆኑ ታውቋል፡፡

ስልጠናውን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት ም/ዋና ኦዲተር ክቡር አቶ ሀጂ ኢብሳ የተሻሻለው  ማኑዋልና ተዛማጅ የአሠራር ሰነዶች በመንግስት ተቋማት ሊኖር የሚገባውን የተጠያቂነት፣ የግልጽነትና የመልካም አስተዳደር አሠራር ለማረጋገጥ መ/ቤቱ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያንጸባርቅ ነው ብለዋል፡፡

አክለውም የክዋኔ ኦዲት በስራ ላይ የሚውል ሀብት በትክክል በስራ ላይ መተግበሩን በማረጋገጥ ሁኔታ ላይ ብቻ የሚወሰን ሳይሆን የመንግስት ፕሮግራሞች ስኬታማነትንና እና የሀብት አጠቃቀምን ውጤታማነት የሚፈትሽ መሆኑን ጨምረው ጠቅሰዋል፡፡

ከሁሉም በላይ መንግስት በሚያከናውናቸው ስራዎች የዜጎች ህይወት መሻሻሉን ማረጋገጥም ጭምር የክዋኔ ኦዲት አላማ መሆኑን የጠቀሱት ክቡር አቶ ሀጂ እነዚህን ጉዳዮች ትርጉም ባለው አኳኋን ለመመለስ የኦዲት አሠራሩን ከወቅታዊ የአሠራር ዘዴዎችና ሀገራዊ ሁኔታን ካገናዘቡ የተለያዩ የአለም አቀፍ የኦዲት ስታንዳርዶች ጋር ማሳለጥ ይገባል ብለዋል፡፡

በአዲስ መልክ የተሻሻለው የክዋኔ ኦዲት ማኑዋል የአለም አቀፍ የኦዲት ተቋማት ስታንዳርድን መሰረት አድርጎ የተዘጋጀና ከእቅድ እስከ ክትትል ያሉ ሂደቶችን ያካተተ መሆኑን በንግግራቸው የጠቀሱት ክቡር ም/ዋና ኦዲተሩ ከማኑዋሉ ጋር የተዘጋጁ ተዛማጅ የአፈጻጸም ሰነዶችም በኦዲቱ ሂደት ወጥ የሆነ አሠራርን የሚያረጋግጡና አላስፈላጊ የስራ ጫናዎችን የሚቀንሱ እንዲሁም የተሻለ የሰነድ አያያዝ እና የአሠራር ጥራት እንዲኖር የሚያደርጉ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ክቡር ም/ዋና ኦዲተሩ አክለውም ስልጠናው በጽንሰ ሀሳብና በተግባራዊ አሠራር መካከል ያለውን ክፍተት ለመሙላት እድል የሚፈጥር መሆኑን ጠቅሰው ዜጎችን ጨምሮ ከቁልፍ ባለድርሻ አካላት ፍላጎት አንጻር ወቅታዊ፣ በመረጃ የተደገፈ፣ ውጤት ሊያመጣ የሚችል እና ወደ ትክክለኛና የተሻለ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ የሚያደርስ የኦዲት ሪፖርት ማመንጨትና  ይህንንም ኃላፊነት በቁርጠኝነትና በሙያዊ ጥረት መወጣት ይጠበቃል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም ሰልጣኞች በቆይታቸው ንቁ ተሳታፊ በመሆን ስልጠናውን እንዲያካሂዱ አሳስበው ማኑዋሉን በማሻሻል ሂደትም ሆነ ስልጠናውን በማዘጋጀት አስተዋጽኦ ላበረከቱ የአውሮፓ ህብረት የቴክኒካል ፋሲሊቲ ዘርፍ አካላት እንዲሁም ለመ/ቤቱ አባላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

OFAG Launches In-Person Training Program on updated Performance Audit Manual and Working Papers

The Office of the Federal Auditor General, Ethiopia (OFAG) of Ethiopia has launched an EU-supported capacity-building training program designed to equip auditors with in-depth knowledge of the newly updated Performance Audit Manual and accompanying Working Papers.

The training will take place over two consecutive rounds from 15–26 September 2025, bringing together auditors from various departments, including Performance and Environmental Audits, Audit Quality Assurance, IT Audit, and Training and Education.

Opening the session, H.E. Mr. Haji Ibsa, Deputy Auditor General for Performance and Environmental Audit Operation, emphasized that the revised manual referring to methodology, methods and tools is now fully aligned with International Standards of Supreme Audit Institutions, marking a significant step in enhancing the overall quality and impact of performance audits.

“This revised manual promotes accountability, transparency, and the effective use of public resources. Most importantly, it ensures that government programs are delivering meaningful and measurable benefits to our citizens,” stated by H.E. Mr. Ibsa.

H.E. Mr. Ibsa also underlined the importance of the training in closing the gap between audit theory and practice, enabling auditors to produce evidence-based, impact-oriented audit reports.

In his closing remarks, H.E. Mr. Ibsa extended his sincere appreciation to the EU Technical Facility Unit, OFAG Performance Audit Working Group, and internal experts for their strong commitment to the revision process and for supporting the successful rollout of this training initiative.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *