News

በስነ ተዋልዶ ጤና እና የልጆች አስተዳደግ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

በስነ ተዋልዶ ጤና እና የልጆች አስተዳደግ ዙሪያ ያተኮረ ስልጠና ከመ/ቤቱ የተለያዩ የስራ ክፍሎች ለተውጣጡ አመራሮችና ሠራተኞች ከታህሳስ 21-22 ቀን 2014 ዓ.ም ተሰጠ፡፡

ስልጠናው በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ ሲሆን  ለሁለት ቀናት  በሁለት ዙሮች የተካሄደውን  ስልጠና የሰጡት ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ሙሉ ጥሩነህ ናቸው፡፡

በስልጠናው የስነ-ተዋልዶ  ጤና ምንነት፣ ስለ ስነ-ተዋልዶ ጤና እውቀት  አስፈላጊነት፣ በአብዛኛዉ የስነ-ተዋልዶ ችግር  ተጠቂ ስለሆኑ  የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የስነ-ተዋልዶ ጤና  ችግሮችና  መንስኤዎች  እንዲሁም መፍትሔዎች  የሚሉ ጉዳዮች ተዳሰዋል፡፡

የልጆች አስተዳደግን በተመለከተም ያለፉት ዘመናት እና የአሁኑ ዘመን የልጆች አስተዳደግ ባህርያት አንድነትና ልዩነት፣ መልካምና  መልካም ያልሆነ የልጆች አስተዳደግ ምንነትና መንስዔ፣ የልጆች  አስተዳደግ የመጨረሻ ግብ እና መልካም ያልሆነ የልጆች አስተዳደግን ለመቅረፍ ስለሚያስችሉ  መፍትሄዎች በስልጠናው ሂደት በስፋት ተብራርቷል፡፡

ስልጠናው በገለጻና ሰልጣኞችን በጥያቄና መልስ በማሳተፍ  የተካሄደ ሲሆን በስልጠናው መጨረሻም ተሳታፊዎች በስነ ተዋልዶ ጤና እና በልጆች አስተዳደግ ዙሪያ የነበራቸውን ግንዛቤ ይበልጥ ያዳበሩበት፣ ጠቃሚና ወቅታዊ ስልጠና እንደነበር ጠቁመዋል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *