News

በስርዓተ ጾታና ማህበራዊ ጉዳዮች አካታችነት ኦዲት ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ

ለፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የስራ ኃላፊዎች በስርዓተ ጾታና ማህበራዊ ጉዳዮች አካታችነት ኦዲት ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ለሶስት ቀናት በአዲስ አበባ የተሰጠው ስልጠና  ከኢትዮጵያ ሴቶችና ህፃናት ልማት ድርጅት ጋር በመተባበር ሲሆን የስርዓተ ፆታና ማህበራዊ ጉዳይ አካታችነት፣ የስርዓተ ፆታ ምላሽ ሰጪነት፣ በጀትና የስርዓተ ፆታ ኦዲት አሰራሮችና ዝርዝር ሂደቶች የሚሉ ጉዳዮች በስልጠናው ተሸፍነዋል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ በስልጠናው መክፈቻ ላይ ተገኝተው የስልጠና ማስጀመሪያ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ስልጠናው በተለይም ዓለም አቀፍ የስርኣተ ጾታ አካታችነት ኦዲት ድንጋጌዎችን ተከትሎ ለመስራትና በኦዲት በሚታዩ ከፍተቶች ላይ ተገቢ የሆኑ የኦዲት አስተያየቶችን ለመስጠት የሚያግዝ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

መ/ቤቱ ከሚያከናውናቸው ኦዲቶች አንዱ የስርዓተ ፆታ አካታችነት ኦዲት መሆኑን ጨምረው የገለጹት ዋና ኦዲተሯ የስርዓተ ጾታና ማህበራዊ ጉዳዮች አካታችነት ኦዲት ስራ በእውቀት መመራት እንዳለበት ጠቁመው ለዚህም ከሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲሁም ከሌሎች በጉዳዩ ላይ ከሚሰሩ ሲቪክ ማህበራት ጋር አብሮ መስራት የኦዲት ስራውን ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ያግዛል ብለዋል፡፡

በስልጠናው ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ሴቶችና ህፃናት ልማት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ አያሌው እጅጉ በበኩላቸው ስልጠናው ከዚህ ቀደም ከመ/ቤቱ ጋር አብሮ ለመስራት በተደረገው ስምምነት መሰረት የቀረበ መሆኑን ጠቁመው ለመ/ቤቱ የኦዲት የስራ ኃላፊዎች በስልጠናው ይዘቶች ላይ ይበልጥ ግንዛቤ ማስጨበጥን ዓላማው ያደረገ ነው ብለዋል፡፡

በስልጠናው 35 ከተለያዩ የስራ ክፍሎች የተውጣጡ የመ/ቤቱ የስራ ኃላፊዎች ተሳታፊ መሆናቸው ታውቋል፡፡

 

OFAG Training to strengthen Audit of Gender & Social Affairs Mainstreaming

The Ethiopian Office of the Federal Auditor General (OFAG) provided training in corporate with the Ethiopian Women & Children Development Organization (WCDO) to build the office’s capacity of auditing activities in the area of Gender & social affairs mainstreaming.

In the training given from October 9-11/2024 for three consecutive days in Addis Ababa, about 35 directors & managers of the office attended the capacity building training, and the Federal Auditor General H.E Mrs. Meseret Damtie made opening speech by addressing the usefulness of the training.

Mentioning the constructive impact of the training, H.E Meseret denoted that the training is very useful to apply global provisions and principles of gender audits effectively and efficiently on the auditing activities of the office.

By indicating the particular role of the Ministry of Women & Social Affairs and other civic associations on the gender and social affairs auditing processes, the Auditor General adds cooperative works with such fitting Institutions can highly make the whole auditing tasks of the office more operational and efficient.

Clarifying specific objectives and advantages of the training, Mr.Ayalew Ejigu, the Director of the Ethiopian Women & Children Development Organization (WCDO), specified in his part of statement that the training was organized and provided based on the previous joint work arrangements of both institutions.

 

   

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *