በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት 21ኛዉ የአለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ተከበረ፡፡
21ኛዉ የአለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ”ወጣቶችን ያማከለ የፀረ–ሙስና ትግል፤ የነገዉን ስብዕና ይገነባል” በሚል መሪ ቃል የመ/ቤቱ አመራሮችና ሠራተኞች በተገኙበት በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በድምቀት ተከብሯል፡፡
በአከባበር ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ጽፈት ቤት ኃላፊ አቶ አወቀ ጤናዉ ሙስና ሀገር ላይ የሚያደርሰዉ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ትልቅ መሆኑን ገልፀው የሙስናን ወንጀል ለመከላከል የሁሉም ዜጎች ሀላፊነት በመሆኑ ይህን መሰል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች በቀጣይነት ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።
የመ/ቤቱ የስነ-ምግባር ባለሙያ አቶ ግርማ አይችሉ በበኩላቸው ሙስና ዓለምአቀፍ ወንጀል ስለሆነ ዓለምአቀፍ ትብብር እንደሚሻ ጠቁመው ይህንን በመረዳት በጋራ በመሆን ሙስናን መታገል እንደሚያስፈልግና ሰራተኛዉ እራሱንና ተቋሙን ከሙስናና ብልሹ አሰራር ሊጠብቅ ይገባል ብለዋል።
“በእለቱ ሙሰናን ከመከላከል አንጻር ከኛ ምን ይጠበቃል” በሚል የፓናል ዉይይት የተደረገ ሲሆን ከመድረኩ በተነሱ ሀሳቦች ላይ ተጨባጭ ልምዶችን በማንሳት ሰፊ ውይይት መደረጉን ከመ/ቤቱ የስነምግባር የስራ ክፍል የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡