News

ለመ/ቤቱ የውስጥ ኦዲተሮችና የንብረት አስተዳደር ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ

ለፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የውስጥ ኦዲተሮችና የንብረት የአስተዳደር ሠራተኞች የንብረት አስተዳደርና ግዢን የተመለከተ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ከነሐሴ 22 እስከ ነሐሴ 24/ 2016 ዓ.ም በመ/ቤቱ የሥልጠና ማዕከል በተሰጠው ስልጠና የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ኦዲተሮች፣ የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና እና የግዥና ንብረት አስተዳደር ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡

ስልጠናው በዋናነት በግዥና ንብረት አስተዳደር አሠራር ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል አሰራሮችና ቴክኒኮችን ለማስጨበጥ ታስቦ መሆኑን ከመ/ቤቱ የትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የውስጥ አቅምን ተጠቅሞ የሰራተኛውን አቅም ለማጎልበት የተለያዩ ስልጠናዎች እየሰጠ ይገኛል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *