ፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የማኔጅመንት አባላት የተሰጠው የአመራርነት ክህሎት ስልጠና የመ/ቤቱን የኦዲት ሥራ ለማሻሻል ጉልህ ሚና አለው ተባለ፡፡
ሥልጠናው ከአፍሪካ የእንግሊዘኛ ተናጋሪ ዋና ኦዲተሮች ማህበር /AFROSAI-E/ በመጡ አሠልጣኞች ከሐምሌ 17-21 ቀን 2015 ዓ.ም ለ5 ተከታታይ ቀናት የተካሄደ ሲሆን የአመራነት ክህሎት ልማት /Management Development Programme/ አካል መሆኑ ተገልጿል፡፡
በስልጠናው ስለ አመራርነት ልማት ምንነት፣ ዓለማ እና ሊዳብሩ ስለሚገቡ የአመራርነት ክህሎቶች፣ ተቋማዊ አቅም ግንባታ፣ ስትራቴጂክ እቅድና አስተዳደር እንዲሁም ኮሙዩኒኬሽን እና በባለድርሻ አካላት ግንኙነት ዙሪያ በአሰልጣኞቹ የግንዛቤ ማስጨበጫ ገለጻ የተሰጠ ሲሆን የሰልጣኞች የእርስ በእርስ ልምድ ልውውጥ የተካሄደበት ነው፡፡
በስልጠናው የተሳተፉ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የማኔጅመንት አባላትም ሥልጠናው የኦዲቱን ሥራ ከመሻሻል ባሻገር የራሳቸውን የአመራነት ክህሎት ለማሳደግ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት ሙያን ለማሻሻልና የሠራተኞቹን አቅም ለማሳደግ በየጊዜው በተለያየ ደረጃ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች እያካሄደ ሲሆን ይህ ስልጠናም የተቋማዊ አቅም ግንባታ አካል መሆኑ ታውቋል፡፡